ግንቦት 24/2017 ዓ.ም \ትምህርት ቢሮ/ በበዓሉ የድርጅቱ መስራቾች፣ የባህር ዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ፣ የባህር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ \ዶክተር/፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ልዩ ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በትምህርት ቤት ጉብኝትና በልዩ ልዩ ክንውኖች ተከብሯል።
ፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ በልበ ቀናዎቹ ካናዳዊያን ጥንዶች ዴቪድ ጅኮስኮ እና ጅና ጅኮስኮ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2015 የተመሰረተ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ባለፉት የ10 ዓመታት ጉዞው በአማራ ክልል ስምንት ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ ከ2መቶ 61 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ 27 ትምህርት ቤቶችን ከህብረተሰቡ እና ከመንግስት ጋር በመተባበር ገንብቶ ከ80 ሽህ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉ ተገልጿል።
ፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ከትምህርት ቤት ግንባታ በተጨማሪ የትምህርት ቤት ግቢን ጽዱና አረንጓዴ በማድረግ ምቹ የመማር ማስተማር አካባቢን በመፍጠር፣ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር እንዲለማመዱ በማድረግና ትምህርት ቤቶች ከአረንጓዴ ልማት ገቢ እንዲያመነጩ በማስቻል በርካታ ስራዎችን ሰርቷል። መምህራንን በማሰልጠን፣ ለተማሪዎች፣ መምህራንና የአካባቢው ማህበረሰብ የአይን ጤና ህክምና በመስጠት፣ በውሀና ስነ ንፅህና ላይ ሲሰራ ቆይቷል።
በ10ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል ላይ የታደሙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ አንማው ቢዘንጋው ፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ከየአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ በመስራት በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ተግባራት ማከናወኑን ተናግረዋል። ድርጅቱ ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶች በሙሉ በግብዓት፣ በሂደት እና በውጤት ሲመዘኑ ደረጃቸውን ያሟሉ መሆናቸውን አቶ አንማው አመላክተዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሾሎጅ መምህርና በፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ስራዎች አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ ድርጅቱ ግልፅ ራዕይ፣ ትጋትና ግልፀኝነት የሰፈነበት አሰራር የሚከተል በመሆኑ በአጭር ጊዜ በጥራትና በአነስተኛ ዋጋ ዘመን ተሻጋሪ ትምህርት ቤቶችን መገገንባት እንዳስቻለው ገልጸዋል።
የባህር ዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ ፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ በባህር ዳር ከተማ ያከናወናቸው ደረጃቸውን የጠበቁ የትምህርት ቤት ግንባታ ስራዎች ትውልድ የሚያመሰግነው፣ ታሪክ የሚያወሳውና የህሊና እርካታ የሚሰጡ በመሆናቸው በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በከተመዋ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከተመዋን የሚመጥኑ እንዲሆኑ ለማስቻል አቅዶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባው በቀጣይ ጊዜያት ከድርጅቱ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አመላክተዋል።
የፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ድርጅት መስራች ጅና ኮስኮ እሳቸውና ባለቤታቸው ዴቪድ ትምህርት ዓለምን ይቀይራል የሚል እምነት ስላላቸው ለሴቶችና ህፃናት ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ መስራታቸውን ገልጸዋል። ምቹ የትምህርት ቤት አካባቢን በመፍጠር ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ባለፉት 10 ዓመታት በርካታ ተግባራት ማከናወናቸውን ተናግረዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation





+5
See insights and ads
Boost post
<img class="x16dsc37" role="presentation" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
All reactions:
42