በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ /ዶክተር/ የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ የሚከተለውን የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል  ክልላዊ ፈተናዎችን በስኬት ለማጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የፈተና ግብረ ኃይል አቋቁሞ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች ማድረጉ ይታወሳል።

 

በመሆኑም በክልሉ በመጀመሪያው ዙር ሰኔ 3 እና 4 የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 5 እና 6 ሲሰጥ የቆየው የስድስተኛ ክፍል ፈተና የፈተና ህግና ደንብን በጠበቀ መንገድ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡

በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ለመፈተን ከተመዘገቡት ተማሪዎች መካከል ከ90% በላይ የሚሆኑ ተፈታኞች ፈተናውን በአግባቡና በሰላማዊ መንገድ ወስደዋል፡፡

ፈተናው ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች  የልፋትና ድካም  ውጤታቸውን ፍሬ የሚያዩበት፤  የክልሉ የትምህርት ስርዓተ ያለበት ደረጃ የሚለካበትና ከዚህ ተነስቶ የወደፊት አቅጣጫ የሚቀመጥበት በመሆኑ በስኬት መጠናቀቁ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ለዚህ ስኬታማነት የደከማችሁ የጸጥታ ግብረ ሃይል አካላት ፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ የመምህራን ማህበር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ባለድርሻ አካላት ሁሉ በራሴና በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

በቀጣይም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሀምሌ 8/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ይሰጣል፡፡ ይህን ፈተና የፈተና ህግ እና ስርዓትን በጠበቀ መንገድ ለማከናወን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ መምህራን፣ ወላጆች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሁሉ እንደከዚህ ቀደሙ  ለተፈታኝ ተማሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር፣ ተፈታኞችን በማጓጓዝ፣ ፈተና የሚሰጥባቸውን የፈተና ጣቢያዎች ደህንነት በመጠበቅ፣ የመልስ መስጫ ወረቀቶች በአግባቡ ወደ ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዲደርሱ በማድረግ የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪየን አቀርባለሁ፡፡

 

ሙሉነሽ ደሴ /ዶክተር/

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

#AmharaEducationBureau

#ትምህርትለትውልድ

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

  1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
  2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
  3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
  4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse

ያግኙን

  1. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
  2. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *