የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለዞንና ወረዳ ትምህርት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ሰኔ 21/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለዞንና ወረዳ ትምህርት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን የቢሮው እቅድ ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ዘመነ አበጀ ገልጸዋል፡፡

 

በክልሉ በተለያዩ የስልጠና ማእከላት ለሁሉም የወረዳና የዞን የትምህርት ቡድን መሪዎች ስልጠና  እየተሰጠ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ የትምህርት ባለሙያዎችን አቅምና ግንዛቤ በማሳደግ የመፈጸም አቅም ለማሻሻል ያለመ  መሆኑን አመላክተዋል፡፡

 

በስልጠናው ላይ የተካተቱት ርዕሰ ጉድዮች የትምህርት ዘርፍ የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ አዘገጃጀት እና የ25 ዓመት ፍኖተ ካርታ፣   በአዲስ የተዘጋጀው የትምህርት አዋጅ፣ የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ አተገባበር፣ አዲስ በተሻሻለው የሙያ ፍቃድ መመሪያ እና አሰራር፣ ለተማሪዎች የስነ አእምሮና የአካል ጥንካሬ እንዲሁም የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠናከር የስፖርት ሊግ አደረጃጀት በትምህርት ቤት፣ ልዩ ልዩ ደንብ፣መመሪያዎች፣ማንዋሎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

 

 

በዋናነት ስልጠናው በአዳዲስ አሰራሮች፣አዋጅ፣መመሪያዎች ፣ስታንዳርዶች ዙሪያ ግልጽነት በመፍጠር፣ የህብረተሰቡን የመልማት ፍላጎት ግምት ውስጥ ያስገባ የጠራና ግልጽ እቅድ በማዘጋጀት ትምህርትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ መሆኑን ተመላክቷል፡፡

 

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

  1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
  2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
  3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
  4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse

ያግኙን

  1. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
  2. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *