************
ሰኔ 10/2017 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ / የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በባህርዳር ከተማ በሚገኙት ፋሲሎ 2ኛ ደረጃ እና መስከረም 16 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ችግኝ ተክለዋል።
በትምህርት ዘርፉ በክረምት በጎ ፈቃድ አግልግሎት ከሚሰሩ ስራዎች ውስጥ አንዱ ትምህርት ቤቶችን ሳቢና ማራኪ ለማድረግ በትምህርት ተቋማት ችግኞችን መትከል ከተያዙት እቅዶች መካከል አንዱ ነው። በትምህርት ተቋማቱ የተተከሉ ችግኞችም የትምህርት ቤቶች ምገባ አገልግሎትን ታሳቢ ያደረጉ ናቸው።
የትምህርት ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከዚህ በፊት ደም መለገሳቸው ይታወሳል።