==============
ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በአማራ ክልል በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚያስተምሩ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ዛሬ በክልሉ በሚገኙ በ10ሩ መምህራን ትምህርት ኮሌጆች የአቅም ግንባታ ስልጠናው መሰጠት ተጀመሯል፡፡
ስልጠናውን በቨርቿል ያስጀመሩት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ባስተላለፉት መልእክት ሀገራችንና ክልላችን ባሳለፍናቸው ሁለት አስርት አመታት በበርካታ ፈተናዎችን አሳልፈዋል የዚህ ፈተና ዋናው ምክንያት ደግሞ የትምህርት ስርአቱ መሆኑን በመረዳት አዲስ ስርአተ ትምህርት ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መገባቱን አስታውሰዋል፡፡
አዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጣነውን የህዝባችን እሴትና ባህል የሚመልስ በአገር በቀል እውቀት የበለጸገ በመሆኑ ብቁ፣ተወዳዳሪና በስነምግባር የዳበር የሰው ሀይል ለማፍራት ለሚደረገው ጥረት ጉልህ ድርሻ እንዳለው አክለው ገልጸዋል፡፡
ስርአተ ትምህርቱ ከተቀየረ ጀምሮ መምህራንን በየደረጃው ትውውቅ ሲደረግ መቆየቱን የተናገሩት ሀላፊዋ አሁን በክረምት የሚሰጠው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የ2018 የትምህርት ዘመንን የመማር ማስተማር ሂደት ውጤታማ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ታጀበ አቻምየለህ መምህራን በትምህርት ይዘቶች ላይ ትኩረት አድርገው በመሰልጠን የመማር ማስተማሩን ስራ ውጤታማ ለማድረግ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው የሚያተኩርው በአምስት የትምህርት አይነቶች ሲሆን ሂሳብ፣እንግሊዝኛ፣አጠቃላይ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት አይነቶች እንዲሁም በትምህርት ቤት አመራር ዙሪያ ትኩርት ያደረገ መሆኑን ከፕሮግራሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ስልጠናው በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ 10ሺህ የሚሆኑ መምህራንና ከ1ሺህ በላይ የሚሆን የትምህርት ቤት አመራሮች ለሁለት ሳምንታት ያህል የአቅም ግንባታ ስልጠናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *