=======================
 በሃገራችን የኪነጥበብ ታሪክ ውስጥ ስማቸውን ጎልቶ ከሚጠቀሱት ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት ደራሲ፣ገጣሚ፣ሀያሲና መምህር አያልነህ ሙላቱ ናቸው፡፡
በከበረ የሀገር ፍቅራቸው የሚታወቁት የጥበብ ሰው በማናቸውም የጥበብ ጥሪዎች ሁሉ በአካል በመገኜት ልምዳቸውን በማካፈል እና በተለያዩ ድጋፎች በመሳተፍ ይታወቃሉ፡፡
ዳንግላ ከተማ የሚገኘውን የህዝብ ቤትመጸሀፍት ዲጅታላይዝ ለማድረግ በርካታ የኮምፒውተር ድጋፍ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ከሰሞኑ በዳንግላ ከተማ የሰሩት ተግባር ደግሞ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ ዜጎች የተማሩበትን አካባቢ እንዲያስታውሱ የሚያደርግ በጎ ተግባር ከውነዋል፡፡
እኒህ የኪነጥበብ ሰው የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት በሚደረገው ርብርብ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት በተማሩበት ዳንግላ ከተማ መንገሻ ጀንበሬ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ጎን የሚገኘውን የመኖሪያ ቤት ቦታ ለትምህርት ቤት ማስፋፊያ እንዲውል መፍቀዳቸውን ከከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እንደታላቁ የጥበብ ሰው ሁሉ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ የቀድሞ ተማሪዎች የተማራችሁበትን አካባቢ በማስታወስ እና የጎደለውን በመሙላት የበኩላችሁን አሻራ እንድታስቀምጡ ጥሪውን እያስተላለፈ ለታላቁ የጥበብ ሰውም ታላቅ ምስጋና ያቀርባል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *