ከ69 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመመዝገብ ወደ ትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ አቅጃለሁ አለ የደሴ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ።
የመምሪያው ሀላፊ አቶ ፍቅር አበበ እንደተናገሩት በ2018 ዓ.ም 69 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እስከ ነሀሴ 19/2018 ዓ.ም በመመዝገብ ምዝገባው ይጠናቀቃል ብለዋል።
በ2017 ዓ.ም አንደኛ ደረጃ ከመቶ ፐርሰንት በላይ እንደነበር እና በቅደመ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ 95 በመቶ እና የሁለተኛ ደረጃ ደግሞ 75 በመቶ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ፍቅር ዘንድሮ ሁሉንም እቅዳቸውን በማሳካት 69 ሺ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን አንስተዋል።
እስከ አሁን ባለው የምዝገባ ሂደት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የመንጠባጠብ ነገር መኖሩን ያነሱት አቶ ፍቅር እስከ ነሀሴ 19/2018 ዓ.ም ምዝገባ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።
ለትምህርት መጀመሩ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረገ ሲሆን በበጎ ፈቃደኞች የት/ቤቶችን አጥር ማሳጠር፣ የመማሪያ ክፍሎች እድሳት፣ የላይብረሪ እና ቤተ መፅሀፍት የማጠናከር እና የማደረጃት ስራዎች ተከውነዋል።
የትምህርት ቤቶችን አቅም ከማሻሻል አንፃር ለመጪው የትምህርት ዘመን 44 አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች ተገንብተው 12ቱን መረከባቸውን ያነሱት ሀላፊው ቀሪዎቹን በቅርብ ቀን ርክክብ ይደረጋል ብለዋል።
መምሪያው ከግል ትምህርት ቤቶች ጋር በጋራ በመስራትና ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ህብረተሰቡ በአገልግሎታቸው እንዲረካ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግሯል።
ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱና በተገቢው ግዜ በማስመዝገብ ልጆቻየውን ወደ ትምህርት ገበታ እንዲልኩ ያሳሰቡት አቶ ፍቅር የመጀመሪያ ቀን ክፍል መስከረም 5/2018 ዓ.ም ይጀመራል ብለዋል ሲል ደሴ ፋና ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *