ነሐሴ 7/2017ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ የትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና ከአማራ ክልል 24 ሽህ የሚጠጉ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ ገልጸዋል፡፡
የሙያ እና ተግባር ትምህርቶችን ጨምሮ በ12 የትምህርት ዓይነቶች የሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናውን በውጤታማ እና ሰላማዊ በሆነ ሂደት እየሰለጠኑ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አቅማቸውን በማዳበር የተማሪዎች ውጤታማነት ለማሻሻል ስልጠናውን በኃላፊነት ስሜት በትኩረት እየተከታተሉ እንደሚገኙ አቶ ደምስ አመላክተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *