ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር እና የሰሜን ጎጃም ዞን የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ የየመምሪያወቹ ቡድን መሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ መምሪያወቹን የሚደግፉ የትምህርት ቢሮ ባለሙያወች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱ የምዝገባ ሂደቱ ያለበት አፈጻጸም፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ያተኮረ ነው።
ውይይቱን የመሩት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ ትምህርት ቤቶች የወላጆች፣ የልዩ ልዩ የማህበረሰብ አደረጃጀቶችን እና የማህበረሰቡን እገዛ ተጠቅመው ሁሉንም ተማሪዎች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት መዝግቦ በማጠናቀቅ ለመማር ማስተማር እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።