ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከዞን እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የትምህርት አመራሮች ጋር የትምህርት ለትውልድ የቃል ኪዳን ሰነድ ስምምነት አካሂዷል።
የቃል ኪዳን ስምምነቱ በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እና በዞን ወይም ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች መካከል የ2018 የትምህርት ዘመን ቁልፍ የውጤት አመልካቾችን ለማሳካት የተዘጋጀ የመግባቢያ ስምምነት ነው።
የፊርማ ስነ ስርዓቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ /ዶክተር/ እና ሁሉም የዞን እና ከተማ አስተዳደር ትሞህርት አመራሮች አካሂደዋል።
በስምምነት ሰነዱ ላይ የፈረሙት የትምህርት አመራሮች የ2018 የትምህርት ዘመን ላይ የተቀመጡ ቁልፍ የውጤት አመልካቾችን በማሳካት ጥራት ያለው ትምህርት ለትውልድ ለማድረስ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *