የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጳጉሜ ሁለት “የህብር ቀን” ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎችና ለአረጋዊያን ድጋፍ አደረገ
========
ጳጉሜ 2/2017 ዓ. ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ለተማሪዎችና ለአረጋዊያን ድጋፍ አድርጓል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርተ ቢሮ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቢሮው በባህርዳር ከተማ ለሚገኙ አረጋዊያን እና አቅመ ደካማ ወገኖች ለበዓል መዋያ የሚሆን የፊኖ ዱቄትና ዘይት ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድጋፍ መርሃ ግብሩ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማእረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ ዶ/ር ባስተላለፉት መልዕክት ለነገ ሀገር ተረካቢ ሀጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል:: ለአረጋዊያ ደግሞ ውለታችሁ አለብን አይዟችሁ በርቱልን ሲሉ አበረታተዋል፡፡
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አብዱ ሁሴን /ዶክተር/ ህብርነት ማለት መተሳሰብ፣ለተቸገሩ ወገኖች መድረስና መረዳዳት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ በተለያዩ ከተሞች በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው ዛሬ በባህርዳር ከተማ የተካሄደው የበጎ አድራጎት ስራ የዚህ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡