የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የጥሬ ገንዘብና የትምህርት ግብዓት ድጋፍ አደረገ፡፡

የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ 700 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የጥሬ ገንዘብና የትምህርት ግብዓቶችን ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ድጋፍ አደርጓል፡፡

የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብይ አበበ አሸባሪው የህውሀት ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት የተጎዱ የትምህርት ተቋማትን ለመደገፍ የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ክፍተትን የለየ ድጋፍ ለማድረግ በወሰነው መሰረት ቢሮው 400 ሺህ ብር የሚገመት የቁሳቁስና 300 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከባቸውን ገልፀዋል፡፡

 

እንደ ኃላፊው ገለፃ ጦርነቱ እንደ ሀገር ኢትዮጲያን ለማፍረስ የታቀደ ስለነበረ ሁሉም ኢትዮጲያውያን ከጫፍ ጫፍ በመዝመት የቀለበሱት ሲሆን አሁን ደግሞ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት የሐረሪ ክልል የበኩሉን እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡

ድጋፉ  የተለያዩ ግብአቶች የተካተቱበት ሲሆን ኮምፒውተር ፣ የኮምፒውተር ቀለም ፣ ፕሪንተር ፣ ወንበር ፣ ብላክ ቦርድ እንደሚገኝበት አቶ አብይ አስረድተዋል፡፡ ድጋፉ አሁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ኃላፊው ከአሁን በፊት በሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች 2 ሚሊዬን ብር የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን አውስተዋል፡፡

 

ድጋፉን የተረከቡት የኮምቦልቻ ሪጆዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳር ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን የሱፍ የሐረሪ ክልል ለወገን አስቦ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ በኮምቦልቻ ከተማ በመገኘት ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ከድር ሁሴን በበኩላቸው የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለመገንባት ያደረገው ድጋፍ ክፍተትን የለዬ መሆኑን ገልጸው ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን የኮምቦልቻ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል፡፡

የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።

 

በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።

 

ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w

በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/

በቴሌግራም https://t.me/anrse

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *