የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤቶች የሚያጋጥሙንን የተማሪዎች መማሪያ መጽሃፍት እጥረት ችግር ለመፍታት በየክፍል ደረጃው ያሉ ሁሉንም የተማሪዎች መማሪያ መጽሃፍት በትምህርት ቢሮው ዌብ ሳይት በመጫን አገልግሎቱን ለመስጠት ጥረት እያደረግን ሲሆን አሁን ላይ የ12ኛ ክፍል የተማሪዎች መማሪያ መጽሃፍት እና ከ1-4ኛ ክፍል የተማሪዎች መማሪያ መጽሃፍትን ከትምህርት ቢሮው ዌብ ሳይት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እያሳሰብን በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ሁሉንም የክፍል ደረጃዎች የተማሪዎች መማሪያ መጽሃፍት በዌብሳይታችን በመጫን ተማሪዎች፣ መምህራንና የትምህርት ባለድርሻ አካላት መጽሃፍትን በቀላሉ ማግኘት የምትችሉበትን ሁኔታ አመቻችተናል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ!!
I think the the primary English text books are not available or inactive, so would you upload gain?