የድጋፍ ርክክብ በተካሄደበት ወቅት የተገኙት በአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላሰተር አስተባባሪ ሙሉነሽ አበበ /ዶክተር/ ኮርድኤድ ወደ አማራ ክልል ከገባ ገና ሁለት አመት ብቻ ቢሆነዉም  በትምህርት ቤቶች ያለዉን የኮቪድ መከላከያ ግብዓት እጥረት ችግር በመረዳትና ቅድሚያ በመስጠት ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል፡፡ የድርጅቱ ድጋፍ ለሌሎች ድርጅቶችም አርዓያ የሚሆን ተግባር በመሆኑ ሌሎች ድርጅቶችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ /ዶክተር/  ኮቪድ 19 በአሁኑ ወቅት እየጨመረ በመምጣቱ ድጋፉ ተማሪዎችንና የመምህራን ደህንነት በመጠበቅ የመማር ማስተማር ስራዉን ለማከናወን የሚያግዝ  ተገቢና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸዉ   ተጠቃሚዎችን በመለየት በአፋጣኝ እንደሚሰራጭ ተናግረዋል፡፡

የኮርድኤድ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ጠና ትምህርት ቤቶች ከረጅም ጊዜ መዘጋት በኋላ የተከፈቱ በመሆኑ ድርጅታቸዉ የኮቪድ 19 መከላከያ ግብዓቶችን ለመደገፍ እንዳነሳሳዉ ተናግረዉ 3 ሚለዬን ብር የሚያወጣ   የአፍ መሸፈኛና የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረጋቸዉን ገልጸዋል፡፡ ኮርድኤድ  በቀጣይም በአማራ ክልል በወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ላይ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ሃላፊዉ አቶ ሳሙዔል  አስታዉቀዋል፡፡

 

8 thoughts on “ኮርድኤድ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት 3 ሚሊዬን ብር የሚያወጣ የኮቪድ 19 መከላከያ ግብአቶችን ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ድጋፍ አደረገ፡፡”
  1. Thank you so much for the availability of the student text books at each grade level!! But, there is no Mathematics and English student text books for grade 7.

  2. የሰባተኛ ክፍል ሂሳብ መፀሀፍ ማውርድ አልቻልኩም በምን መልኩ ማግኘት እችላለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *