በአማራ ክልል የሚገኙ አስር መምህራን ትምህርት ኮሌጆች የኮሌጅ ዲኖች፣ የአካዳሚክ ኮሚሽን አባላት፣ የክልልና የኮሌጆች የመምህራን ማህበር አመራሮች በተገኙበት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በፍኖተ ሰላም ከተማ አካሂዷል፡፡

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ /ዶክተር/ መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ኮቪድ 19 ያሳደረውን ተጽዕኖ ተቋቁመው የ2012 የትምህርት ዘመን ተመራቂ ተማሪዎችን በማስመረቃቸውና ትምህርት በማስጀመራቸው መልካም አፈጻጸም መሆኑን ገልጸዋል፡፡  የኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ኮቪድ 19 ያሳደረውን ተጽዕኖ በመቋቋም ትምህርት እንዲቀጥል ላደረጉት አስተዋጽኦ ቢሮ ኃላፊዉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ከመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር ከመስራት በተጨማሪ ኮቪድ 19 ወደ ህብረተሰቡ እንዳይሰራጭ ግንዛቤ በመፍጠር፣ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ በመስጠትና የማቆያ ማዕከል በመሆን  የማህበረሰብ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

በግምገማ መድረኩ የኮሌጆች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ስፊ ዉይይት ተካሂዶበታል፡፡

በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የሚነሱ የመልካም አስተዳደርና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎችን ለመመለስ ቢሮው የረጅምና አጭር ጊዜ እቅዶችን አቅዶ እየሰራ መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ ልሳነወርቅ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡

መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ኮቪድ 19 ተከላክሎ መማር ማስተማሩን እንዲያስቀጥሉና የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት እንዲገነቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

 

 

 

 

One thought on “የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂደ፡፡”
  1. በጥንካሬና በድክመት ምን ተነሣ? በተለይም በኮሌጅ የሚሠሩ የትምህርትና ሥልጠና ባለሙያዎች የደረጃ ማነስ፣ ወደ መምህርነት የማደግ ጥያቄ፣ ትምህርት ቢሮ ያሉ አካላት የሚፈፅሙት አድሎ ፣ የኮሌጅ ዲኖች ከፕራክቲከም ስምሪት ጋር ተያይዞ የሚመዘብሩት ገንዘብና ባለሙያው ተቀምጦ የዲኖች መዞር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *