በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ምክንያት ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ተማሪዎች መማሪያ የሚሆን የደብተርና እስክብሪቶ ድጋፍ ተደረገ፡፡
===========================================
አሸባሪው የህውሃት ቡድን በአማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች በፈጸመው ወረራ ምክንያት ወላጆችንና ህጻናትን አፈላቅሏል፡፡ በርካታ የመንግስት ተቋማትን የግለስብ ሃብትና ንብረት ዘርፏል አውድሟል፡፡
ህጻናት ለነገ የህይወታቸው ስንቅ የሚሆነውን ትምህርት ለመማር የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት እንዳያጋጥማቸው ለማገዝ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለባለሃብቶች፣ ለተቋማት፣ ለድርጅቶችና ግለሰቦች አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ ጥሪ አቅርቦ ነበር፡፡
ይህን ጥሪ የተቀበሉት የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሁለት መቶ ደርዘን ደብተር፣ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሁለት ሽህ ደብተርና አራት መቶ እስክብሪቶ፣ አባይ ህትመት ራሱ ያመረተውን አንድ ሽህ ስምንት መቶ ደብተር፣ የአካባቢ ደን ጥበቃ ባለስልጣን ከሰራተኞቹና ከተቋሙ ያሰባሰበውን ሰባ ሶስት ደርዘን ደብተርና አስር ባኮ እስክብሪቶ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስረክበዋል፡፡
ድጋፉ ህጻናት በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ውጭ እንዳይሆኑ፣ በተባበረ ክንድ ድህነትን ማሸነፍ እንድምንችልና ወራሪው ሃይል የአማራን ህዝብና ኢትዮጵያን ማንበርከክ እንደማይችል መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ማተብ ታፈረ /ዶክተር/ ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ በትምህርት ማህበረሰቡ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

By awoke

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *