የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች በመደበኛና በማታ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን እጩ መምህራንን አስመርቀዋል።
=============================
በዛሬው እለት የጎንደር፣ በጌምድር፣ ከሚሴ፣ እንጅባራ እና ደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጆች በመደበኛና በማታ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ያስመርቁ ሲሆን የፍኖተ ሰላምና ደብረ ብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ባለፈው ሳምንት አስመርቀዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሙያዎች ሁሉ እናት በሆነው የመምህርነት ሙያ በመመረቃቹህ እንኳን ደስ አላቹህ በማለት ልባዊ ደስታውን ይገልጻል፡፡ ተመራቂዎች በተማራችሁበት የሙያ መስክ ያገኛችሁትን ሙያዊ እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ስነ ምግባር የተላበሰ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ በማፍራት ክልላችሁንና ሃገራችሁን እንድታገለግሉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *