የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ ( ዶ/ር) እና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኃላ የመሰረት ደንጋይ አስቀምጠዋል ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ ( ዶ/ር) እንደገለፁት የአዳሪ ትምህርት ቤት መገንባቱ የተሻሉ ተማሪዎች ሙሉ ጊዜያቸው እንዲጠቀሙ ያግዛል ብለዋል።

በአመለካከት በአስተሳሰብ በእውነት የተሻሉ መምህራን ለአዳሪ ትምህርት ቤቶችን እንደሚመደቡ ጠቁመዋል።
ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን መገንባት ለትምህርት ጥራት የጋራ ርብርብ በማድረግ ትውልድን የመገንባት ስራ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አሳሰበዋል።
በክልሉ 3 ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በ4 ቢሊዮን ብር እንደሚገነቡ የገለፁት ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ትምህርት ላይ በልዩ ትኩረት መሰራት እንደሚገባ ጠቁመዋል መንግሥታዊ መንግታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ ባለሀብቶች ፣ ኮሌጆች ፣ዲያስፖራዎች ለትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ግንባታው የሚገነባው በዳሽን ቢራ እና በጎንደር ዩንቨርስቲ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ግንባታው በፍጥነት ተገንብቶ ወደ ስራ እንዲገባ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) አሳስበዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ በበኩላቸው ሀገር የምታድገው በትምህርት በመሆኑ ዛሬ መሰረት ደንጋይ የሚቀመጠው በትምህርታቸው ተወዳዳሪ የሆኑ ከማንኛውም አካባቢ መጥተው የሚማሩት ትምህርት ቤት ነው ብለዋል።

ጎንደር አዳሪ ትምህርት ቤት በአፄ ሀይለ ሰላሴ ዘመነ መንግስት መኖሩን ያስታወሱት ከንቲባው
በእውቀት በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ በትኩረት መሰራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ትውልድን ለመገንባት ትምህርቶች የራሳቸውን ድርሻ መኖሩን አንስተው ፤የትምህርት ቤቶችን ገፅታ ለመገንባት ደግሞ ባለሀብቶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማድረግ ትውልድ ላይ መሰራት እንደሚገባቸው ከንቲባው ተናግረዋል።

ለአርሶ አደር 2.3 ሚሊዮን ብር ካሳ በተከፈለበት 4.6 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባ መሆኑን አቶ ባዩህ ተናግረዋል።
ግንባታው እስኪጠናቀቅ የአካባቢው ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደረግ ከንቲባው አሳሰበዋል።

 

“ትምህርት ለትውልድ”
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *