አንጻራዊ የሰላም መሻሻል በታየባቸው የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ መጀመራቸው ተገለጸ፡፡
=====================================
ሚያዚያ 19/2016 /ትምህርት ቢሮ/ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደግሰው መለሰ አንጻራዊ የሰላም መሻሻል በታየባቸው የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ ከ360 በላይ ትምህርት ቤቶች ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡
ቢሮው የባከነውን ጊዜ ለማካካስ እንዲቻል የይዘት ማጣጣም ፕሮግራም በማውጣት
ለትምህርት ተቋማት መላኩን አቶ ደግሰው ገልጸዋል፡፡ መማር ማስተማር የጀመሩ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
ትምህርት ቤቶቹ የጀመሩትን የመማር ማስተማር ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉና ሌሎች ስራ ያልጀመሩትን ስራ ለማስጀመር ህብረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በድርቅና ተያያዥ ስራዎች በተጎዱ አካባቢዎች በሚገኙ 442 ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ከ221 ሽህ በላይ ተማሪዎች በመንግስት፣ በአለም ምግብ ድርጅት /WFP/ እና በሌሎች አጋር ድርጅቶች አማካኝነት የትምህርት ቤት ምገባ እየተሰጠ መሆኑን አቶ ደግሰው መለሰ ተናግረዋል፡፡ ምገባ በሚከናወንባቸው ትምህርት ቢቶች የተማሪዎች ማቋረጥና ማሳለስ መቀነሱንና የተማሪዎች ውጤትም መሻሻል መቻሉ ተገልጿል፡፡ የትምህርት ቤት ምገባ የበለጠ ለማጠናከር ማህበረሰቡን እና ባለ ድርሻ አካላትን ተሳትፎ አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ አቶ ደግሰው አመላክተዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *