===========
ሀምሌ 03/2016 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ዛሬ የጀመረውን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመላው ማህበረሰብ ባስተላለፉት መልእክት ወላጆች የልጆቻቸውን የልፋት ፍሬ የሚያዩበትና የነገ ተስፋቸውን የሚተልሙበት መሆኑን ተረድተው ተፈታኝ ተማሪዎችን በማበረታታት፣ ፈተናው ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅ ከትምህርት አመራሩ ፣በአካባቢያቸው ስራውን ለማስተባበር ከተመደቡ የፀጥታ አካላት፣ የፈተና አስፈጻሚዎች እንዲሁም መላ የትምህርት መዋቅር ጋር በመስራት ወገናዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ሁሉን አቀፍ ድጋፍና እርብርብ ማድረግ ይገባል ያሉት ዶ/ር ሙሉነሽ ተማሪዎች ሲጓጓዙ፣ፈተናቸውን አጠናቀወ ሲመለሱ ያለምንም ችግር ወደ ቤተሰባቸው እንዲቀላቀሉ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች የድርሻቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸውም አክለው ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች እንደመሆናቸው መጠን ራዕያቸው እውን እንዲሆን ሁሉም አካላት ፈተናውን የሚያደናቅፉ ማነኛውንም ተግባራት በመታገል ማህበረሳባችን በርትቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ትምህርት ፖለቲካ አይሆንም ሊሆንም አይገባም ያሉት ዶ/ር ሙሉነሽ ማንኛውም አካል የትውልድ ቅብብሎሹን ለማስቀጠል ይረዳ ዘንድ የትምህርት ስራችንን ሊደግፉ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ፈተናው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅና የፈተና መልስ መስጫ ወረቀቶች ተሰብስበው ወደ ማዕከል እስከሚደርሱ ድረስ መላው የክልላችን ህዝብ ተማሪዎች በተረጋጋ ስነልቦና እንዲፈተኑ በማበረታታት፣ የተማሪዎችንና የወላጆች እንዲሁም የመምህራንን ስነልቦና የሚረብሹ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ባለመቀበል የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆች ተስፋ እንዲፈነጥቅ ልንረባረብ ይገባል ሲሉ ዶ/ረ ሙሉነሽ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *