የትምህርት ለትውልድ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በደቡብ ጎንደር ዞን የስማዳ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት “በትምህርት ነገን ዛሬ መስራት” በሚል መሪ ቃል የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት “ትምህርት ለትውልድ የንቅናቄ መድረክ” እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስማዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ጥላሁን
ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ሙህራን መፍለቂያ መሆኗን ገልፀዋል።
እንደ ክልል ፅንፈኛው ሀይል የተማረ ትውልድ እንዳይፈጠር እና አማራ ክልል “የመሃይም ሙዚየም” እንዲሆን እየሰራ ይገኛል ብለዋል አቶ እንዳልክ።
ዋና አስተዳዳሪው እንደገለጹት የመማር ማስተማር ስራው ከገጠመው ስብራት እንዲወጣ እና እንዲቀጥል በጋራ ርብርብ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በንቅናቄ መድረኩ ሱፐርቫይዘሮች ፣ ርዕሰ መምህራን ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የቀበሌ ዋና አስተዳዳሪዎች እና ሌሎችም ባለ ድርሻ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ መሰረት እባቡ የመነሻ ፅሁፍ እያቀረቡ ነው።
#የስማዳ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት”