ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ከህብረተሰቡ ጋር የጋራ መግባባት መፍጠር ይገባል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር፣ ሰሜን ሸዋ ዞንና ደብረ ብርሐን ከተማ አስተዳደር ጋር የትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ ማጠቃለያና የቀጣይ አቅጣጫ የሰጡት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ የትምህርት ዘርፉ በጸጥታ ችግር ውስጥ ሆኖ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ መላው ማህበረሰብና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ዶክተር ሙሉነሽ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ክልላዊና ብሄራዊ ፈተና ለሚወስዱ የ6ኛ፣ 8ኛና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ኃላፊዋ አሳስበዋል።
የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን መመዝገብ፣ ማስተማር፣ ማብቃትና ማጠናቀቅ የትምህርት ዘመኑ የትኩረት ነጥቦች ሆነው ሊሰሩ እንደሚገባ ተመላክቷል።
ጥር 18/2017_ አዲስ አበባ
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse





+3