የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ማስቀጠል ይገባል
ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ
ሚያዝያ 22/2017_ ደሴ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ፣ ዋግኽምራ ብ/አስተዳደር፣ ኦሮሞ ብ/አስ/ዞን፣ ደሴ ከተማ አስተዳደር፣ ኮምቦልቻ እና ወልዲያ ከተማ አስተዳደር ትምህርት አመራሮችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር የዘጠኝ ወር ስራ አፈፃፀሙን በደሴ ከተማ እየገመገመ ነው።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ለትምህርት ስራ ስኬት ሁሉም እርብርብ ማድረግ እንዳለበት ገልፀው የደሴ ከተማ አስተዳደርም ለትምህርት ስራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ተናገረዋል።
በግምገማ መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ የትምህርት ስርዓቱ በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎች እየተፈተነ መሆኑን ገልፀዋል። በሁለት አመቱ የክልሉ ሰላም ችግር ከ4.5ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ተገልጿል።
ትምህርት ትውልድ የሚቀረፅበት ተቋም በመሆኑ ለዚህ ስራ ውጤታማነት ሳይሰለቹ፣ ለፈተናዎች ሳይበገሩ፣ መስራት ይጠይቃል ብለዋል። ሆኖም ግን ችግሩን ተጋፍጠን ባለመፍታት በችግሩ የምንቀጥል ከሆነ ግን ዩኒቨርስቲዎች ላይ የምናስመርቃቸው ተማሪዎች አይኖሩም፣ ኮሌጆቻችን አደጋ ውስጥ ይገባሉ። የትውልድ ቅብብሎሽ ይቋረጣል፤ በአጠቃላይ የአማራ ክልል ህዝብ በሁሉም ዘርፎች የነበረው አስተዋጽኦ እየጠፋ ይሄዳል። ነገር ግን በችግሩ ሳንበገር ከሰራን በአጭር ጊዜ በችግሩ የደረሰብንን ተፅዕኖ ማካካስ እንችላለን። ይህንን ማድረግ የምንችለው ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ከተባበርን ነው ብለዋል።ችግሩን ተቋቁመን ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ ለትምህርት ቤቶች ግብዓቶችን ማሟላት፤ ትምህርት የህብረተሰቡ አጀንዳ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የትምህርት ስራችንን ውጤታማ ለማድረግ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ማስቀጠል፤ ክልል አቀፍና አገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ድጋፍ ማጠናከር፣ ለ2018 የትምህርት ዘመን ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቅ እንደሚገባ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ አሳስበዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *